Monday, May 16, 2016

ለማን አቤት እንበል…?

እባካችሁ… እባካችሁ… እባካችሁ… እኛ በቃ አልቻልንም! ተሰቃየን! ፈተና ሆናችሁብን እኮ! ለማን አቤት እንበል፣ የት አባታችን ሆነን እሪሪ እንበል? ቆይ እሺ የት ሄደን "ዷ" ብለን እንፈንዳላችሁ? ለናንተ ስንል የት "ብን" ብለን እንጥፋ? አገር እንቀቅ? በውቅያኖስ እንዋጥ ? ወደ በረሃ ተሰደን፣በጥላሸት ቀቢ ወንበዴዎች ካራ እንታረድ? የነብሰስጋ  የስቃይ ፈተና ሆናችሁብን እኮ! ቆይ ስቃያችን ለናንተ አልታወቃችሁም እንዴ ? አድናቆት የጋረደው ስቃያችን አልተገለፀላችሁም? ካልተገለፀላችሁ ግልፅ እንዲሆን እንደግመዋለን…

ከምታሳዩን ስቃይ አይበልጥምና እንደግምላችኋለን … ልብ በሉ! አስተውሉ! ወጥመድ ተጎናፅፋችሁ  ባየናችሁ፣ ባሰብናችሁ ቁጥር ነብሳችን ትሰቃያለች፣ ጋዝ እንደ መጠጠ ቃጫ ትንበለበላለች፣ እንደሻማ ትቀልጣለች…እሺ በቃ… ትችላላችሁ አምነናል። አሁንም አይበቃችሁም?።እኛ ወጣት ወንዶች በወጥመዳችሁ ነጋ ጠባ ባለመያዝ ተጋድሎ ተጋግጠናል … ከዚህ በላይ ምን እንሁንላችሁ …? ያሸነፉት አካል ማጥቃት ጀብዱነት መሰላችሁ? አይደለም!! ወይስ ሽንፈታችን አልታወቃችሁም? ካልታወቃችሁ እንደግመዋለን… ተሸንፈናል…  ቆይ እናንተ በኛ የነብስና ስጋ ፈተና ስቃይ የምታተርፉት ነገር ምንድ ነው? ተወልደን እትብታችን በተቀበረበት፣ ጥርስ ነቅለን… ዘለን ቦርቀን ባደግንበት…ቀዬ ውስጠ ሰላም ታሳጡን? ምንስ ቢሆን የአንድ አገር፣ የአንድ ሰፈር፣ ከፍተኛ…፣ ቀበሌ… ገበሬ… ማህበር… ልጆች አይደለንም? በአንድ አይነት ባህልና አስተዳደግ ታነፅን አላደግንም እንዴ? አንድ አይነት የልጅነት ጨዋታዎች አልተጫወትንም፣ ትላንት አፈር ቅመን ጭቃ አቡክተን አድገን ዛሬ ደርሳችሁ በነብስና ስጋ ፈተና ጦር አፈር ከድሜ ታስግጡን? ለምን እንዲህ ይሆናል!… ለምን… ለምን… ለምን… እሱስ ይወደዋል? … ብንሸሻችሁ ማትሸሹን፣ወዴትም ብንዞር ማናጣችሁ፣ በሳር በቅጠሉ … በስራ ቦታ ፣በታክሲ ላይ፣በሀይገር ላይ፣በመንገድ ላይ፣በ ቀንም… ማታ… በህልማችን… ሮጠን ማናመልጣችሁ፣ አረ! ምን ጉድ ናችሁ…?! ለናንተ ስንል ከቤት አንውጣ? በዚህ በነደደ ኑሮ እናንተን ፈርተን ስራ አንስራ? ረሀብ ይግደለን! ይህንን ነው የምትፈልጉት? በሻትናችሁ መጠን ከአንዱ እየወጣን ነው? ወቅቱን በመጥፎ ስሜት እየወደቅን ነው!ቆይ በስንቱ እንውደቅ እኛ… በሚኒስትሪ፣ በማትሪክ፣ በኑሮ፣ በቃል ፈተና ፣በመሰናክል ፈተና፣ በመስክ ፈተና… ካንዱ ጫፍ እስካንዱ ጫፍ በውድቀት ፈተና በሞላው ምድር ላይ የወደቅነው አይበቃምና ነው። እኛ ወጣት ወንዶች ወድቀን… ወድቀን… ልናልፈው ያልቻልነው ፈተና የምትሆኑብን … አረ የገላጋይ ያለህ! ተውን!

አረ በህግ አምላክ! ህጉ ለናንተ አይሰራም? በነብስና በስጋችን የምትለኩሱብን ሽብር … በፀረ ሽብር አዋጁ አይመለከተውም ያለው ማን ነው? ኡፍፍፍፍፍ…ተቃጠልን እኮ ባካችሁ…!

<<ምንድነው እንዲህ ያማረራችሁ?>> ከተባለ ምሬታችን የዘመኑ ሴቶች ናችሁ ነጥቡ አራት ነው። አዎ የስቃያችን መንስኤ  የዘመኑ ወጣት ሴቶች ናችሁ …  ለዚህ ሁሉ መንጨርጨር ያበቃችሁን።

  በእኛ በወጣት ወንዶች ላይ በነብስና በስጋችን ጭስ አልባ ጦርነት አቀጣጥላችሁብናል… ከዘመኑ ኑሮ በላይ ከብዳችሁናል…  መታገስ አቅቶናል … ተፈጥሮ የቸራችሁን ገላ በአግባቡ ሸፍኑልን …አዎ በአግባቡ! ይሸፈን። ሰው እንዴት በጤናው ከፀጉር እስከ ጥፍሩ ስቶኪንግ ይለብሳል? በዘይት እንደተዘፈዘፈ ስስ ሊጥ ሰውነት ላይ ተለጥፎ የእንብርትን ስርጉድ ዳና የማይሰትር፣  የጨርቅ ወጥመድ፣ የምትለብሱ ሴቶች። አዎ! ምሬቴ እናንው ናችሁ! ማንም አይደለም። ተከናንበናል ብላችሁ ነው? አፍረተ ገላን እንደ Hd ካሜራ … ቅልብጭ አድርጎ የሚያሳየውን… ስድ ጨርቅ…የጨርቅ አተላ…  የምትለብሱት?  በአይሁድና በምዕራባውያን ሴራ በጨርቅ በተተበተበ ወጥመድ ወድቃችሁ፣ ወጥመድ ሆናችሁብናል… ለስውር ሴራቸው ሲሉ ስልጣኔ አድርጋችሁ እንድትወስዱት ጫና ያሳደሩባችሁ የምዕራባዉያን ወጥመድ ነው። ለኛ ለወጣት ወንዶችና ሴቶች፣ በናንተው ገላ ላይ የተጠመደ ዝርክርክ ስብዕናና ማንነት ላይ የሚጥለን የጨርቅ ወጥመድ። ሁላችንንም የሚያጠምድ።

እባካችሁ በተለይ በተለይ ሙስሊም እህቶቼ፣ በአባያ ስም እየለበሳችሁት የሚገኘው ልብስ  አረ ምን ልብስ… በእምነት ሽፋን የተጠመደ የጨርቅ ወጥመድ ነው ይሄ! ገላ ላይ ተለጣፊ የጨርቅ ወጥመድ እልም ያለ ወጥመድ! የሚገርመው እኮ የምታስጠብቡት ነገር… እንኳን አስጠብባችሁት እንዲሁም የሰውነት ቅርፅን ሳየት ከበቂ በላይ ነው። እርቃናችሁ የጥላሸት ዱቄት ላይ የተከባለላችሁ እንጂ ጥቁር  ልብስ የለበሳችሁ የማያስመስለው … አባያ የምትሉት የጨርቅ ወጥመድ! ደግሞ አባያ ብለው ሠየሙት እኮ… የአባያን ክብር የሚያጎድፍ … የጨርቅ ልምጥምጥ። ስስ ገላችሁ ላይ እንደ እባብ እየተልመጠመጠ ወደ እኛ የፍትወት መርዙን የሚረጭ! የአይን ወጥመድ! አለማየት ባንፈልግ እንኳ በግድ እየሳበ እንድናይ የሚያደርገን በጨርቅ የተተበተበ መተት!ነው። በእርግጥ ስትለብሱት ለእንቅስቃሴያችሁ ምቾት ይሰጣችሁ ይሆናል፣ እኛን ግን የህሊና ምቾት እየነሳችሁን ይገኛል። ከየትኛውም ባህል፣ እምነት፣ ወግ ልማድ …  ያልተገኘ ክፉ የጨርቅ ወጥመድ! ብዙ ወጣት በፈተና የሚለበልብ ወጥመድ! እምነትን የሚሸረሽር፣ ማንነትን የሚያረክስ፣ ስዕብናን የሚያቀጭጭ የጨርቅ ወጥመድ!  እባካችሁ ለምቾትና ለአድናቆት ብላችሁ ወጥመድ አትሁኑብን! ለጊዜው wow ተብሎ ይደነቅላችሁ ይሆናል ፣ ነገ የክብራችሁን… ዋጋ የሚያሳንስ!የሚያረክስ የጨርቅ ውዳቂ ነው። ውይ እሷ እኮ አለባበሷ ቅጥ አልባ ነበር … እያለ የሚያሳማችሁን የታሪክ ቅርስ ይሆንላችኋል። ለኛም እንደዛው። እናም እባካችሁ!! በዚህም በመጪውም አለም ሁላችንንም የሚያከስረን ተግባር ስለሆነ ሀይ ልንለው ይገባል።

No comments:

Post a Comment