"የስራ … አቡጊዳ…"
#ሳteናw
…በማዕከአዊ ስታቲስቲክ ባለስልጣን ትመና መሰረት ሀዋሳ የ119,623 ሰው መኖሪያ ስትሆን ከነሱም ውስጥ 60,378 ወንዶች 59,245 ሴቶች ሆነው ተተምነዋል።
… በኔ ግምታዊ ትመና መሰረት 25 ሺህ የሚሆኑት ጥርሳቸው ቡኒ ሲሆን 35 ሺህ የሚሆኑ የአዋሳ ቺኮች የሰውነት ቅርፃቸው ውብ ነው…
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የአዲስ አበባው የገና ባዛር አለቀ። ቀጥሎ በአዋሳ የሚደረገው ባዛር በነበረን እቃ ላይ አንዳንድ እቃዎችን ጨምረን ወደ ደቡብ ኢትዮጲያ ርዕሰ ከተማ ሀዋሳ ነካነው። … በአዲስ አበባው ባዛር እንደኛው ባዛር ከሚሳተፉ ሰዎች ተግባብተን ስለነበር በአዋሳው ባዛር ላይ ዳግም ስንገናኝ በደንብ ተላምደን ደስ የሚል ህብረት ፈጥረን አሳልፈናል። አዋሳ ትርፋማ በሚያሰኝ ሁኔታ ባንሰራም አንዳንድ አዝናኝ ገጠመኞች አሳለፍንባት።
(በነገሬ ላይ አዋሳ ከ1998 ቡሃላ፣ ጠንካራ እድገት ያሳየች ቢሆንም፣ ስያሜዋ በንባብ ላልቶ ሀዋሳ ሆኗል። ሀዋሳ በሲዳምኛ ትልቅ ሀይቅ የሚል አቻ ትርጉም አለው።)
ለአይኔ አዲስ ያልሆነችው አዋሳ ከዚህ ቀደም ከማውቃት የበለጠ ውብ ሆና ጠበቀችኝ። ከጥቂት አመት በፊት አሸዋማ የነበረው ውስጥ ለውስጥ መንገዶቿ በኮብል ስቶን ተቀውጠዋል።(ኮብል ስቶኑን ያያሁት በባዛሩ ይሁን ከዛ ቡሃላ በሄድኩበት አጋጣሚ አርግጠኛ እይደለሁም) ብቻ የመልከዓ ምድሯ አቀማመጥ ለጥ ያለ ሜዳ የሆነችው የደቡቧ ፈርጥ ከኮብል ስቶን ጋር በደንብ ማች አድርጋለች።
አዋሳ ከራስጌዋ የታቦር ተራራ ከግርጌዋ ከተንጣለለው ሀይቋ ጋር በየጎዳናው መሀል የተተከሉ ዘንባባዎቿ እና የኮረዳዎቿ ውብ የሰውነት ቅርፅ ጋር ተደማምሮ እውነትም ውብ ምድር ያስብላታል። ሌላው ደግሞ አዋሳ ከተማ ተወላጆችን፣ በመመልከት ብቻ የምትለይበትን መለያ ከተማዋ ችራቸዋለች። ጥርሳቸው፣ ሳይቅሙ ሳየጨሱበት ወደ ቡኒነት ተቀይሯል። ተወልዶ ያደገባቸውን ሰው እንደዚህ አይነት መለያ ከቸሩ ከተሞች ሌላኛዋ ናዝሬት ነች። መንሴውም በድሮ ጊዜ ለመጠጥ የሚውለው ውሃቸው ነው አሉ። አሉ ነው፣ አሉባልታ። በመርካቶ ጥርስ የሚያበላሹት ነገሮች… ጣፋጭ ነገሮች ፣ጫት መቃም፣ ሲጋራማጨስ እና፣ ከባድ ቦክስ፣ ናቸው። በማዕከአዊ ስታቲስቲክ ባለስልጣን ትመና መሰረት ሀዋሳ የ119,623 ሰው መኖሪያ ስትሆን ከነሱም ውስጥ 60,378 ወንዶች 59,245 ሴቶች ሆነው ተተምነዋል። በኔ ግምታዊ ትመና መሰረት ሀምሳ ሺህ የሚሆኑት ጥርሳቸው ቡኒ ነው። ሀምሳ ሺህ የሚሆኑ የአዋሳ ሴቶች የሰውነት ቅርፃቸው ውብ ነው። ከአዋሳ ከሚገርሙኝ ነገሮች አንዱ የሔዋንያን ቅርፅ ነው። በለው! ምንድንው ቆይ ቅርፃቸውን እንዲህ አሳ ያስመሰለው፣ ለአሳ ቅርብ ስለሆኑ ይሆን? ከየትኛውም ከተማ አይን የሚንከራትት ቅርፅ ያለው አዋሳ ነው። ወጣቱ ብቻ መሰለህ? እነማሚም ጭምር ፍዴያቸው አስማት ነው። በአብዛኛው ጋቢናቸው ግን እንደኋላቸው አይደለም። … በአዋሳው ባዛር ከታዘብኳቸው ነገሮች ጥርሳቸውና፣ ሼፓቸው ነው።
ገጠመኝ ①
በአንዱ ቀን ይህ ሆነ። በአዲስ አበባ ባዛር ላይ የተግባባነው አንድ ልጅ፣ በሀዋሳ ምሽት በፒያሳ… ስንዛዟር ከሩቅ ሼፗ የሚመስጥ ሴት ተመልክተን ስናደንቅ በመሃል ልጁ አፏጨላት። ሰምታው ስትዞር። በእጁ ነይ ብሎ ጠራት። አላቅማማችም ወላ አልተሽኮረመመችም መጣች። መምጣቷስ ባክከፋ!! ስትመጣ ከሩቅ በተመለከትነውና ከገመትነው ወጣትነቷ ላይ ሰላሳ አመት የጨመረች ሆና መምጣቷ ነበር።
"አቤየት!!" ብላ በምልክት ወደ ጠራት ጓደኛችን አፈጠጠች፣ማለቴ አፈጠጡ። እሳቸው ልበል እንጂ አንቺማ ክብራቸውን ማሳነስ ነው። ለነገሩ እሜትዬ እራሳቸው ናቸው ክብራቸውን በአለባበሳቸው ያሳነሱት። (እንዲህ አይነት እምቢ አላረጅም አለባበስ በአዲስ አበባም ይታያል። እድሜ ከሄደ ቡሃላ ማጌጥ መልበስ አግባብ አይደለም ሳይሆን፣ እድሜን ያገናዘበና በወጉ ቢሆን ስታይል አለው።) ሴትየዋ አቤት ሲሉ መጡ… ጠሪው ጓደኛችን የሚለው ቢጨንቅ ቢጠበው፣
"ታደሰ ኢንጆሪ ሆቴል፣ እግሬ እስኪቀጥን ብፈልግ ብፈልግ አጣሁት… ብሎ በሩ ላይ የቆመበትበትን ታደሰ እንጆሪ ሆቴል ቦታውን ጠየቃቸው…
"ይኸው" ብለው አጠገቡ ያለውን ሆቴል አሳዩት።
"ውይ ይቅርታ ልብ አላልኩትም ነበር።"ብሎ ተንተባተበና መለሰ። ሴትየዋ ብትፋታንም… ለተወሰነ ቀን የሳቅ ምንጭ ሆነ ጀለሱካችን።
ገጠመኝ ②
ከስራ ቡሃላ ማታውን እኛ ወደ አልጋ በጊዜ ገብተን እንተኛለን። አሰሪያችን በሁለተኛው የሌሊት አጋማሽ ሽርብትን ብሎ በተኛንበት ይገባል። ይህ ሁኔታ አንድ ሁለት ቀን ሲደጋገም አብሮኝ ከሚሰራው ልጅ ጋር እኛስ ከማን እናንሳለን? ግፋ ቢል ከደሞዛችን ቢቆረጥ ነው ብለን ከተኛንበት ተነስተን ወደ ከተማ ነካነው። የሂሳብ ብር እኔ እጅ ላይ ቢሆንም በራሳችን ብር ከአንድ መቃሚያ ቤት ገብተን ምርቅን ምንቅር ስንል አምሽተን ወጣን። ሁለታችንም ፍሬሽ ቀመቴዎች (ለጫት አዲስ) ስለነበርን ምርቃናው ጉድ ሰራን ጓደኛዬና እኔ መንገድ ላይ ለሽንት ቆምን።
ከቆምንበት ስፍራ ትይዩ፣ አንድ ጨለማ ቅያስ ነበር። ጀለስካ
በመሃል አንዳች ነገር ከጨለማው ውስጥ አየና…
"አየሃቸው እዛጋ ኪስ እየተደራረጉ ነው?" አለኝ።
"አረ! የታሉ?" አልኩት።
"ይኸው" ብሎ አንድ ፅልመት የዋጠውን ቅያስ ጠቆመኝ።
ቅያሱ ሙሉ በሙሉ ጨለማ ሲሆኑ ከጀርባው የሚያቋርጠው መንገድ ፏ ያለ ብርሃን ነበር። ልክ ሲኒማ ቤት ቤት በለው ቅያሱን!! ተቀምጠህ ፊልም እየሾፈተርክ ከስክሪኑ አንፃር የሚንቀሳቀስ ሰው ስትመለከት ቅርፁን ብቻ እንደምትመለከው ነገር ነበር፣ ያየውን… ተቃቅፈዋል ብሎ ከግምት፣ ይሁን ከሽፍደት…
"ያው አይታዩህም?"
"አው አው አንተ… አልኩት"። የሚሳሳሙ ሰዎች ይሁን የተቃቀፉ በእርግጠኛ አይደለሁም ብቻ ጥቁርና ሰፊ የተቃቀፉ የሚመስሉ ሰዎች ወደኛ እያዘገሙ ይቀርባሉ። ቆይ ተደብቀን እንያቸው ተባብለን። እኛ ወዳለንበት ብርሃን እስኪደርሱ ቆመን መጠበቅ ጀመርን። "ቆሙ!!" እየተሳሳሙ መሆን አለበት። አዎ አልኩት እርግጠኛ ባልሆንም። የማይደርስ የለም ወደ ብርሃኑ ደረሱ…። ምን ዋጋ አለው እስካሁን የሚሳሳሙ ሰዎች ናቸው ብለን የጠበቅነው ጥቁሩ ነገር … ባለቤቱ የጣለውና እከክ የወረሰው ግድንግድ ፈረስ ሆኖ አረፈው። በራሳችን እየሳቅን የተደበቅንበትን ስፍራ ለቀን ጉዟችንን ቀጠልን። አለቃችን ሳይቀድመን ቀድመን ወደ ማረፊያችን ደረስን። ፈጣሪ ሲረዳን ልክ እንደገባን መጣ። ሌላ ቀን በእንቅልፍ አቅላችንን ስተን የሚያገኘን ሰውዬ… በምርቃና ፈጠን አገኘን። እስካሁን አልተኛችሁም? … አዎ። ቢጠረጥረንም ዝሎ ስለመጣ ዘሎ አልጋውላይ ወጥቶ ዝም ብሎን ተኛ። በማግስቱ ጠዋት አርፍደን ሲያየን ጥርጣሬው አደገ። አሁንም ምንም አላለም።
ባማግስቱ በአዋሳው ባዛር የቀኑን ስራ ጨርሰን ወደ አልቤርጎ እንደሚሄድ ሆነን… ወደ አንድ ባር ነካነው። ገባን። ብልጭ ድርግም እያለ አይን ከሚያጭበረብረው ዲም ላይት ጋር ተጨማምሮ የሙዚቃው ድምፅም ናላ ያዞራል። አዛ ፈሳሽ አየለበለብን ሳለ አሰሪያችን 4:00 ላይ በኔ ሞባይል ደወለ። "ወይኔ ደወለ"። አልኩት ለስራ ባልደረባዬ። አታንሳው አለኝ። ማንሳት ብፈልግስ በዛ ጩኸት እንዴት ላንሳው። ሳላነሳ ዝም አልኩት። ቆይቶ ደግሞ ደወለ። ባሩን ለቅቄ ድምፅ ወደማይሰማበት ስፍራ እሮጥኩ ወጣው። የባሩ አስተናጋጅ ሂሳብ ሳልከፍል የማመልጥ መስሎት ከኋላዬ ሊከተለኝ ሲል… ሰዒድ ይዞ ሁኔታውን ነገረውና ተመለሰ። ፀጥ ያለ ስፍራ ብደርስም የሙዚቃው ድምፅ የሌሊቱን ፀጥታ ሰንጥቆ በስሱ ያስተጋባል። አነሳሁት።
"ሀሎ"
"ሄለው የት ናችሁ ?"
"እ… አዛው ማለት ኳስ አያየን?"(በጊዜው የአፍሪካ ዋንጫ ይካሄድ ነበር።)
"የማንና የማንን" መስቀለኛ ጥያቄ መሆኗ ነው።
"ሴኔጋል ከኮትዲቯር" አልኩ አፌ እንዳመጣልኝ።
"ነው? እሺ መጣው ብሎ!" ስልኩን ዘጋ። ሮጬ ወደ ባሩ ተመለስሁና። ጓዴን ጠርቼ ና ቶሎ ውጣ ወደ ቤርጎ እየሄደ ነው ብዬው ሂሳባችንን ዘግተን እየተጣደፍን ወጣን። በስልክ ያወራነውን ነገርኩት።
"ጨወታዉ የማንና የማን አልከው?"
"ሴኔጋል ከኮትዲቯር"
"ወይኔ የሴኔጋል ጨዋታ እኮ 1:00 ላይ ነበር የታየው!! ይህን ያውቃል እኮ።)
"በቃ ተደገመ እንለዋለና" ልለው አልኩና ድንጋጤያችን ስላየለ ትቼው… እንደ ማራቶን ተወዳዳሪ ጭር ባለው የአዋሳ አውራ ጎዳና ሳምባችን እስኪፈነዳ መሮጥ ያዝን አልቤርጎ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረሰን። አሰሪያችን ደመቅ ደመቅመቅ ብሎ ኮንትራት በያዛት ባጃጅ ደረሰብን።
"እ! ሴኔጋል ብሎ በዛ ብራቅ ድምፁ ፀጥታ በነገሰባት የአዋሳ ምድር አንባረቀ። ቁና ቁና እየተነፈስን በድንሆነን ቀጥ አልን። "ወይኔ ገንዘቤ! ወይኔ ገንዘቤ! ብሎ ከልቡ ያልሆነ ኡኡታውን አስነካው።" እኛ ምንም አላደረግንም ብለን ምለን ተገዝተን ልናሳምነው ብንሞክርም ሊያምነን አልቻለም። ጥንድ አልጋ ባላት ቤርጎአችን ገባን። እንደገባን ወቀሰዋን ጀመረ "ሰላም ልጅ ነህ ብዬ! ምንም አታውቅም ብዬ ካሼር ባደርግህ ሮንድ ትዞርልኛለህ? ለነገሩ ማን ይህን ሀሳብ እንዳነሳው አውቃለው። ብሎ ወደ ጓዴ አየ።
"አረ እኔ አይደለሁም" ሲል ታሱን ተከላከለ። "ዝም በል አንት አይነ ደረቅ፣አላውቀህ መስሎሃል የአብነት ወሮ በላ፣የአብነት አይን ቀርጥፎ የበላህ ዝም በል መልስ እንዳትሰጠኝ። ሰኢድ አያጉረመረመ አንገቱን ደፋ። ከብዙ ወቀሳ ቡሃላ አለቃችን ደክሞት ሲተኛ። እኛም ተኛን። ምስኪን ነው። በማግስቱ ግን የምሽቱን ሁኔታ ረስቶት ዋለ። ምሽቱን ወደ ቤርጎ ልንሄድ ስንል አብረን ነው ምንሄደው ጠብቁኝ አለን። ቤርጎ እጃችንን ይዞ ሊያስገባን ነው ብለን ብንገምትም ልክ አልነበርንም። ምርጥ የፍየል ጥብስ እራት ጋበዘን።
አዋሳ ምድር የክርስቲያና የሙስሊም ልኳንዳዎች ልየነታቸው ላይ ብዙም ትኩረት አይደርጉም። ለምን? ብዬ ስጠይቅ አብዛኛው የከተማው ነዋሪ የኘሮቴስታንት እምነት ተከታይ በመሆኑ ነበር። ከእራቱ ቡሃላ አንድ ባር ይዞን ገባ። በቃ ከኔ ጋር ይዝናኑ ብሎ ነው ብለን አሰብን። የባሩ እስተናጋጅ መጣ። "አለቃ ቀድሞ ለኔ አንድ ጉዳዩና ለነሱ ሁለት ሚሪንዳ!" ሲል አዘዘ። እኔና ጓዴ ዞረን በግርምት አየነው? ምናባህ ታፈጣለህ? ልትጠ አማረህ ደረቅ!" ሲለን ለንቦጫችንን ዘረገፍን። አለቃ ባላየ ላሽ። ሚሪንዳረውን ስንጨርስ ሌላ ደግሞ ለኛም ድጋሚ ሚሪንዳ።"እንደ አራስ ሚሪንዳ ላይ በላይ አስግቶን ከባሩ ወጣን። ወደ አልቤርጎ ስንሄድ ሆዳችን እየተንበጫበጨ እንደ ውሻ በየ እርምጃው ለሽንት እየቆምን ደርሰን ገባን።
በአዋሳ መስቀል አደበባይ በተባለው ቦታ ላይ በሸራ እንደ በተሰራልን አዳራሽ ውስጥ ፣ በትንንሹ የተከፋፈሉ ጊዜያዊ የባዛር ሱቅ ከአዋሳ ሐሩር የአየር ፀባይ ጋር በሙቀት ተቀቅሎ መዋሉ ከባድ ነበር። ሙቀቱ በኛ በወንዶች ላይ ተፅኖው ባይጎላም እንደኛው በሸራው ውስጥ ታምቀው የሚውሉ ሴቶችን ለከፍተኛ ሽፍደት ዳረጋቸው። ወንዶች በምርቃና ሲፈዙ፣ ሴቶች ሲወቀጡ ሲገቡ መቅበጥበጥ፣ ማስካካት መጯጯህ አበዙ። በተለይ ከአጠገባችን ሱቅ ለሽያጭ የተቀጠረች የጥቁር ቆንጆ፣ ከኔ ጋር ተላምዳ ወደ መደብራችን ብቻዬን ስሆን ጠብቃ ከች በማለት ጀመረች። የሼፗን ቅርፅ የሚያጎሉ ልብሶች ለብሳ እየመጣች እግር አበዛች።የሰውነቷ ቅርፅ አስማት ነበር። አለ አደል ንካኝ ንካኝ እቀፈኝ እቀፈኝ የሚል ሰውነት። የመልኳን ጥቁረት የሰውነቷ ቅርፅ ደብቆታል። ነብሴ ለካ ሽፍዱ ብላ ኖሯል! እኔ መች አወኩ ባውቅም ለአቅመ አዳም እንጂ ለአቅመ ድፍረት ገና ነበርኩ። የመርካቶ ልጅ በተለይ የኛ ሰፈር አብዛኛውን ጊዜ የሚገናኘው ከንግድ እንጂ ከቺክ ስላልሆነ ቶሎ ተላምዶ ደሽ ለማድረግ ጊዜ ይገድላል። መቃለድ፣ መላፋት እንደ መጀመር አለች፣ ውይ ሙቀቱ እያለች ከላይ የለበሰችውን በአጠገቤ ሳታፍር ማውለቅ አበዛች። እኔ የአይን ሻወር ከመውሰድ ውጪ እጄን እንዳላነሳ እንዳልኩት ድፍረት አለነበረኝም በዛላይ እኔ የአዋሳ ስቄ ጫት ቅሜ በሁኔታዋ ስቄ ስቄ ዝም ብቻ ስላት፣ ከፊት ለፊታችን ያለው ባለ ሱቅ ሁኔታችንን ታዝቦ … ሰውነቱን አይተሽ ነው? ጩጬ እኮ ነው! ሲላት አንድ ቀን ሰማሁት። ከዛ በሁላ እሷም እግር ማብዛቷን አቆመች።"ይሄኔ ነበር የባነንኩት። ወይኔ ብዬ ተቆጨው። ምክኒያቱም ባዙሩ ወደ መቋጨቱ ነበር። ወደ አዲስ አበባ ተመለስን። ቀጣይ ጉዟችን ወደ ነቀምትና ጊምቢ ተጓዥ ባዛር ሆነ!…
ወገሬት!!
No comments:
Post a Comment