Monday, May 29, 2017

"ነ ሻ ጣ ው የ ት ሄ ደ ሳ ?"


#ሳteናw

እኔ ምለው "ምነው የረመዳን ነሻጣ እንደበፊት አልሆን አለሳ? " እኔ ብቻ ነኝ ወይስ ሁላችሁም ታዝባችሁታል?" (በነገሬ ላይ እያወራውህ ያለሁት ስለ መርካቶው የረመዳን ድባብ ነው።) ስለሌላው ስፍራ አላውቅም። እኔ በበኩሌ ምንም ረመዳን ረመዳን  አልሸትህ አለኝ። ይህ ትዝብቴ ረመዳኑ ሳይገባ የታዘብኩት ነው። በረመዳን ዋዜም ከተማዋን፣ በየብስ ላይ የሚነዱ ሄሌኮፕተር ይመስል በጄነሬርና በመንዙማ ድምፅ እየቀወጡ የመንዙማ አልበም የሚሸጡ ታክሲዎች አላየሁም። የባሮ ቅጠል፣ድንብላል፣ የሊጥ መዳመጫ በዘንቢል አንግበው ሰፈሬ የሳንቡሳ ስጋ ለመግዛት የሚመጡ እህት እናቶች እስኪናፍቁኝ ድረስ ደብዛቸው ጠፋኝ። ወይስ ዘንቢል ትተው እንደ ስማርት ፎን፣ ባሮና ድንብላሉን በቦርሳቸው መያዝ ጀምረው ይሆን?" ታዲያ ምን ልበል ቢጨንቀኝ እኮ ነው? መስገጃ ይዞ በነሻጣ ወደ አንዋር መስጊድ የሚሄድ ሰው ማየት ዘበት ሆነ። ለምሽቱ ድባብ ቁንጮ የነበረው የአንዋር መስጊድ የተራዊህ ድምፅ፣ አምና እንደቫየረብሬ ት በድንግዝግዙ ይሰማ ነበር። ዘንድሮ ጭራሹኑ ሳይለንት ላይ ሆኗል። አንድ ወዳጄን ይህን በተመለከተ ስጠይቀው የሰጠኝ መልስ ተከታዩ ነበር … "ድምፁ በውስጥ መስመር እንጂ ለሁሉም በሚሰማ መልኩ ላወድ ስፒከር መደረግ ስለተወ ነው" አለኝ። "ለምን" ብዬ አልኩት "ያው ሰሚ ስላጣ ነዋ። ድሮ ግቢው ጠቦት፣ በየ አስፋልቱ ላይ አንጥፎ የሚሰግደው ሰው ቁጥር ተመናምኖ ተመናምኖ በመስጊዱ የሚሰግዱት ኢማሙና መዓዚኑ ብቻ እስኪመስልህ ድረስ ባዶ ሆኗል። ደግሞ አንዋር ከመስጊድነት ወደ ፖሊስ ጣቢያነት ከተከረበተ ውሎ አድሯል። አንተ በሩ ላይ ያለውን ታጣቂ ሀይሎች ውክቢያ ስትሾፍ፣ መስጊድ በር ላይ ሳይሆን ቂሊንጦ በር ላይ ያለህ ሊመስልህ ይችላል። ይህም ጣልቃ ገብነት በምመኑ ቁጥር መቀነስ ላይ የራሱን አስተዋፅዎ አበርክቷል፣ አድሜ ለእንትና!!  በዛ ላይ አንዋር መስጊድ ዙሪያ የነበሩ መኖሪያ ቤቶች በመልሶ ማልማት ሰበብ በሙሉ ከአካባቢው ዲሌት ተደረዋል፣ ታዲያ ሰሚ በሌለበት ለምን ሀይል ይባክናል?"ሲል የራሱን መላምት አካፍሎኛል። በእርግጥ መርካቶ የረመዳኑ ድባብ መደብዘዝ የጀመረው ዘንድሮ ባይሆንም፣ ጭራሽ ድብዝብዝ ብሎ ያገኘሁት ግን ዘንድሮ ነው።መርካቶ በመልሶ ማልማት ዘመቻ፣ እየፈረሰች እየተቆራረሰች፣ በፊት ያሞቁ ያደምቋት የነበሩ በዙሪያ የነበሩ መኖሪያ ቤቶቿ፣ ዛሬ ፈርሰው ባልተጀመሩ በታጠሩ ፍርስራሽ ሜዳዎችና፣ ተጀምረው ባልተቋጩ ህንፃዎቿ ተከባ ወና ወና የሚሸት አየር ይነፍስባታል። ድሮ በሱሁር ሰዓት የሙሳፊር ድምፅ የምትሰመሰማው፣ ዛሬ እንደ በረሃ ነፋስ የሚያፏጭ የአየር ድምፅ ሆኗል። የተረዊህ ድምፅ ከላይ እንዳልኩህ፣ ነው። ብቻ ይንንና ያሳለፍከውን ዘመን ስታነፃፅር፣ አንዳች ከባድ ነገር እንዳጣህ ይሰማሃል። ዘንድሮን ትተህ ድሮን በናፍቆት እያሰብክ ትቆዝማለህ!! ሌላማ ምን ታደርጋለህ?? አስኪ ያግራው።
ወገሬት!!