Saturday, August 20, 2016

አይ መርካቶ

አይ መርካቶ!

አገር ከየጎራው ወጥቶ
አንቺን ብሎ ነቅሎ መጥቶ
ግሣንግሱኘሡን ጓዙን ሞልቶ
ኅልቄ መሣፍርትሽ ፈልቶ
ባንቺ ባዝኖ ተንከራቶ
እንደባዘቶ ተባዝቶ
ተንጠራውዞ ዋትቶ ዋትቶ

አይ መርካቶ!

የምድር ዓለም የእንጀራ እናት
ላንዱ ርካሽ ለሌላው እሣት
ላንዱ ፍትሃት ላንዱ ምትሃት
ላንዱ ሲሳይ ላንዱ ፍርሃት
ላንዱ ተስፋ ላንዱ ስጋት
የግርግር የሆይታ ቋት

አይ መርካቶ!

ያንዱን ወስዶ ላንዱ ሰጥቶ
ያንዱን ገፍፎ ላንዱ አብልቶ
አንዱን ነስቶ ላንዱ አድልቶ
ስንቱን ፈርቶ ስንቱን ሸሽቶ
ባፈ ጮሌ ተሸልቶ

እይ መርካቶ!

ቢያዋጣ ወይ ባይዋጣ
ከስንቱ ተንጣጥቶ ጣጣ
ተነታርኮ ተገዛግዞ
ተብለጥልጦ ተበዛብዞ

መርካቶ ያገር ድግሱ
የገጠር ስንቅ አግበስብሱ
ለከተሜው ለአባ ከርሱ
በትሬንታው በአውቶብሱ
በቁሳቁስ ግሳንግሱ
ለቱጃር የጥጋብ ቅርሱ
ለኔ ቢጤው የቀን ጉርሱ
አባ መስጠት እጦት ቢሱ

አይ መርካቶ!

ተሻምቶ ተገበያይቶ
ወይ ተፈራርሶ ተጣልቶ
በእንካ ስላንቲያ ተማትቶ
አንዳንዴም ተፈነካክቶ
ተመራርቆ ተስማምቶ

አይ መርካቶ!

የኤስፔራንቶ ቋንቋ ሀገር
ያ ሲነገር ያ ሲሰበር
የስንቱ ልሳን ሲቀመር
ያንዱን ሲያከር ያንዱን ሲያቀር
ያንዱን ሲያውስ ያንዱን ሲያስቀር
ያ ሲደቀል ያ ሲፈጠር
የልሣን ሸማች ለብቻ
ከዕቃው ጭምር በስልቻ
ሲመዠርጥ እንደ ግቻ
ቶሎ በል ቶሎ በል ብቻ
ዝግ በሉ እማይባልበት
መርካቶ የአንደበት ፍላት
ግርግር እሚባልባት
ክርክር እሚሞቅባት
ደላላ እሚያውጅባት
ቸርቻሪ እሚተምባት
ሌባ ላብክን እሚያልብባት

አይ መርካቶ!

ላንዱ ምድር ላንዱ ጣራ
ያ ሲዘረፍ ያ ሲደራ
ያ ሲወስን ያ ሲፈራ
ያ ሲሸሽግ ያ ሲያወራ
የንግድ ጠፍ ወይ ያዝመራ
የነጋዴ ምጥ መከራ
የከበረ እንደመረዋ፣ረብጣ አፍኖት ሲያስገመገም
የከሰረ እንደ ፈላስፋ፣ በቁም ቅዠት ሲያልጎመጉም
የኔ ቢጤም ጠብሻ መቶት፣በየጥሻው ሲያስለመልም
ቸርቻሪ ዝርዝሩን ቋጥሮ፣ቅንጣቢውን ሲቃርም
የወር ሸማች ስንቁን ጭኖ፣ ሲመርቅና ሲረግም
ማጅራት መቺ ከጀርባው፣ ጥሻውን ዘሎ ሲያዘግም
ከዚህ በርሮ እዚያ ሰብሮ፣ ያዝ ሲባል ሲሸሽ ሲጣጣር ካማኑኤል ከራጉኤል፣ ሾልኮ ዶሮ ማነቂያ ዳር ከመስጊድ እስከበረንዳ፣ ከአራተኛ እስከ ነፍስይማር
የኡኡታው የጡሩንባው፣የጩኸቱ የፊሽካው ሳግ
የሰው የመኪና የከብት፣ የፍግ የቁሳቁስ ትንፋግ
ሲገፋተር ሲገሻለጥ፣ ላቦት ለላቦት ሲላላግ
ትንፋሽ ለትንፋሽ ሲማማግ
አባ ሽብሩ መርካቶ፣ ያለውን አጣጥቶ
የሌለውን ከሌለበት፣ እስጎልጉሎ አስወጥቶ
ስንቱን ከዳር ዳር አዛምቶ
በግድም በውድ አስማምቶ
አገር ካገር አካቶ
ሁሉን አቀፍ ባይ መርካቶ
ያቻችለዋል አሻምቶ
አይ መርካቶ!

ከክቡር ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

Friday, August 12, 2016

"አጭሩ የህይወት ታሪኬ እንደ ኢትዮጲያ ታሪክ በፀፀት የተሞላ ነው"


#ሳteናw  

  ቤቲ ምን ማለቷ ይሆን? "አጭሩ የህይወት ታሪኬ እንደ ኢትዮጲያ በፀፀትና የተሞላ ነው!!" ስትል?።
… ከቅርቡ ታሪካችን ጀምሬ እስከ ሩቁ የአክሱም ዘመነ መንግስት ድረስ ተጓዝኩ…

  አፄ ሀይለስላሴ ከአምስት አመቱ ሽሽት ሲመለሱ አርበኞችን መተናኮል ያዙ። የጎጃሙን ስመጥር አርበኛ በላይ ዘለቀን ያልምንም ርህራሔ ዙፋን ተዳፈረ በሚል በስቅላት ቀጡት። አገር ተደናገጠ። የሚገርመው ነገር የያኔውን ቅጣት ያስፈፀመው የያኔው የክቡር ዘብ መቶ አለቃ የወደፊቱ ጄነራል መንግስቱ ነዋይ ነበረ። "ኢትዮጲያ ወንድ አይብቀልብሽ!" አለ በላይ። የስቅላት ሸምቀቆው በአንገቱ ሲገባ። የገመዱ ቋጠሮ ማንቁርቱ ላይ በማረፉ አሟሟቱ ስቀይ በዛበት። አትፍረድ ይፈረድብሃል! አለ የሀገሬ ሰው። ጄነራል መንግስቱ በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ምክኒያት በላይ በተሰቀለ ልክ በ21ኛው አመት ዕጣው ደረሰው። ሸምቀቆው በአንገቱ ሲገባ ታዲያ ቋጠሮውን በጀርባዬ በኩል አድርጉልኝ ብሎ ተማፀነ። እንዳለውም ተደርጎለት ሞተ።

ይሄን ይሆን የፀፀት ታሪክ ያለችው?  

… ኢትዮጲያ የአድዋን ጦርነትን በድል የጨረሰችው ሶስት ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነበር። አፄ ሚኒሊክ ቢፈልጉ አስመራን መያዝ ይችላሉ። ራሷን አድዋን የመያዝ ያህል ቀላል ነበር። "ምክኒያታቸውም በትክክል ይህ ነው" ብሎ የፃፈው እስካሁን አልተገኘም። የጦርነቱ መዘዝ የነበረው የውጫሌ ስምምነት አሁን ተሽሯል። ነገር ግን መረብን ሳይሻገሩ ቀሩ። በሽንፈቱ የተሸበረው የጣሊያን መንፈስ መለስ አለ። ይኸው ዛሬ ሰንኮፉ ለኛ ትውልድ ተረፈ። በ40ኛው አመት በመርዝ ጋዝ ተለበለብን። ጀብሃና ሕዝባዊ ግንባር ሀርነት ኤርትራ ከተፈጠሩ ወዲህ ደግሞ መበጠስ ከጀመርን 13ኛው ዓመታችንን ያዝን። አድዋ ላይ ካለቁ አባቶቻችን በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ህይወት ከፈልን…

ቤቲ የፀፀት ታሪክ ስትል ይሄን ይሆን?

  ቴዎድሮስ በ50ኛው አመታቸው ላይ የሞቱ ወጣቱ ንጉስ ናቸው። ለንግስና ማዕረግ የበቁት በእሳቸው አነጋገር ከትቢያ ተነስተው ነው። ጭልጥ ካለ በረሃ ወደ ከተማ አቅጣጫ አያሌ ውጊያዎችን አሸንፈው ነው። በአገዛዛቸውው የኢትዮጲያን ህዝብ ብዙ አዳዲስ ነገሮች አሳዩት። መዓከላዊ አገዛዝ… መሠረተ ልማት … አንድ ለአንድ ጋብቻ… ዝርዝሩ ብዙ ነው። ቤተክርስቲያን ሲነካኩ ነገር መጣ። ለአንድ ደብር ሁለት ቄስ፣ ሶስት ዲያቆን፣ ሌላው ወደ እርሻ!! ያለጊዜው የወሰዱት እርምጃ ነበር። ጎርፍ የነበረው ወታደራቸው ከዳቸው። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ከእንግሊዝ ጋር አይንና ናጫ ሆኑ። ጄነራል ናፒር ሊወጋቸው ሲመጣ አምስት ሺህ ወታደር ብቻ ነበራቸው። ኋይለኛው ንጉስ በገዛ እጃቸው ወደቁ።

  አፄ ዩሃንስና ራስ አሉላ መቼም ለጣሊያን መቅሰፍቱ ናቸው። ዶጋሊ ላይ አምስት መቶውን ወታደር ሲጥ አደረጉት። አሉላ ከአድዋ ድል ቡሃላ ሲገርማቸው ይህን ተናገሩ። "እንዲያው እናንተ ጣሊያኖች፣እናንተ መሸነፍ እኛ ማሸነፍ አይሰለቸንም" ልበል?!። አሉት አንዱን ምርኮኛ ጄነራል በንቀት። በ1881 የጣሊያን ጦር ከምፅዋ አስመራ አመራ። አፄ ዮሀንስ ክተት አውጀው ሊገጥሙት መረብን ሲሻገሩ ካህናት ጣልቃ ገቡ። "ጃንሆይ! ምንም ጣሊያን ጠላታችን ቢሆን እኮ እንደኛው ክርስቲያን ነው። እንዴት የክርስቲያንን ደም ያፈሳሉ?። ይልቅ እስላሙ ጠላታችንን ደርቡሽን አይወጉልንም? ዮሀንስ አመንትተው አመንትተው ፈታቸውን ወደ መተማ አዞሩ። አልተመለሱም። በደርቡሽ አልሞ ተዃሽ ተመተው ወደቁ። ከሞቱ ቡሃላ አንገታቸው ተቆርጦ አምድርሀማን ገባ… "

ቤቲ የፀፀት ታሪክ የምትለው ይሄን ይሆን?

"በ16ኛውና በ17ማው ክፍለ ዘመን ለኢትዮጲያ የመከራ ዘመናት ነበሩ። ኢትዮጲያውያን ሰይፍ መዘው እርስ በእርስ የተራረዱበት ዘግናኝ ጊዜ። ግራኝ አህመድና አፄ ልብነ ድንግል አገር ባዶ ባድማ እስከ ምትሆን ድረስ ተላለቁ። ቤተስኪያንና መስጊዶች ወደሙ። ይህ አልበቃ ብሎ … መሳፍንት ሌላ የእክቂት ድግስ ይዞ መጣ። መሀለኞችና ዳረኞች፣ መሀለኞ ከመሀለኞች፣ ዳረኞች ከዳረኞች … ተጨፋጨፉ።ይህ ጋብ ሲል ደግሞ የቅባትና የፀጋ መስቀሉን ጥለው ጎራዴ አነሱ። ጎንደር፣ጎጃም፣ ሸዋና፣ ትግራይ ጎራ ለይተው ተገዳደሉ። እስከ 16–17ኛው ክፍለ ዘመን ከስልጣኔ ጋር እኩል የተራመደችው ኢትዮጲያ ቀጥ ብላ ቆመች። ዳፋው አሁንም አለ።  አክሱም ፅዮን ማሪያም ቤተከርስቲያን በ10ኛው ክፍለ ዘመን የንግስት ሳባ የወርቅ ጫማ ተሰርቆ ከተማዋ በአሰሳ ታመሰች። ካህናት አንድ የቆሎ ተማሪን ጠርጥረውት በመጨረሻም አመነ። ለምን ሰረቅክ? ለማንስ ሠጠኸው? መረመሩት። "ዮዲት የምትባል አንድ ፈላሻ ቆንጆ ፍቅር ይዞኝ አምጣልኝ ስትለኝ ሰርቄ ሰጠዋት።" ብሎ መለሰ። ወጣቷ ዮዲ ት ተይዛ ለፍርድ ቀረበች። ግራ ጡቷ ተቆርጦ እንድትባረር ተደረገ። ሲራራ ነጋዴ ሲና በረሃ ወስዶ ጣላት። ዮዲት40 ሺህ ጦር አሰልፋ  ከአመታት ቡሃላ አክሱም ተመለሰች። አክሱሞች ረስተዋት ስለነበር በጭፈራ ተቀበሏት። ልክ የአክሱምን መሬት ስትረግጥ ሰይፏን ከአፎቱ መዘዘች። ምድሩን ቁና አደረገችው። አክሱም ጉልበት ከዷት በአፍጢሟ ተደፋች። ሰልጣኔዋም አከተመ።

ቤቲ ይሄን ከሆነ የፀፀት ያለችው ምን እንከን ይወጣላታል? ምንም!ምንጩ የሱፍ አበባ ነው ከሀብታሙ አለባቸW። እንደታነበው ግብዣዬ ነው!!
ወገሬት!!