Sunday, September 4, 2016

ፈዋሽ ስም

"ፈዋሽ… ስም"
#ሳteናw

… ባልንጀራችሁ እንዲፈወስ ከፈለጋችሁ ትዕዛዜን በጥሞና አድምጡ። የማዛችሁን ሳታዛንፉ ፈፅሙ። የዚህ ሰው ፈውስ ከምትጠሉት ሰው ስም ጋር የተቆራኘ በመሆኑ አንድ ሺህ ጊዜ  ስሙን ጠርታችሁ በስኒው ውሃ ላይ እንትፍ ትሉበታላችሁ… በዚህ ከተስማማን ህክምናዬን መጀመር እችላለው…
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

  የጎንደር ትልቁ ገበያ ቅዳሜ ገበያ ይባላል። ከገበያው ጎን አንድ መስጂድ ይገኛል። ከመስጂዱ ጀርባ የኛ ሰፈርነው። አካባቢው በሙሉ ቅዳሜ ገበያ በሚል ይታወቃል። የኛ ሰፈር ደግሞ በተለየ ሁኔታ የሸህ ለጋስ መንደር ትባላለች።

  ሼህ ለጋስ የአባቴ አባት ናቸው። በ1905 ዓ/ል ሸህ ለጋስ ጫካ መንጥረው ከአካባቢው መስፈራቸውን አባቴ ሲያወራ ሰምቸዋለው። ሲበዛ ጀግና ነበሩ። በራሳቸው ስልት ለእስልምና ሰርተዋል በዛላይ ዓሊምና የባህል ሕክምና አዋቂ ናቸው። ይህን ክህሎታቸውን እስልምናን ለማገልገል ተጠቅመውበታል። በዚህ ረገድ በርካታ ታሪኮች ይነገሩላቸዋል።

  አንድ ቀን በጎንደር ታዋቂ የሆነ ቄስ በእባብ ተነድፎ ለሕክምና ከሳቸው ዘንድ መጣ። የጎንደር ቀሳውስት እስልምናን እንደሚጠየፉ ሸሁ ጠንቅቀው ያውቃሉ። በተለይ መሀመድ (ሰዐወ) የሚለውን ስም በጭራሽ መስማት እንደማይፈልጉ። ሸሁ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ቄሱን ለህክምና ይዘው የመጡ ቀሳውስትን ነቢዩን ስም እንዲጠሩ ፈለጉ። ውሃ በሲኒ አቀረቡና ባልንጀራችሁ እንዲፈወስ ከፈለጋችሁ ትዕዛዜን በጥሞና አድምጡ የማዛችሁን ሳታዛንፉ ፈፅሙ። የዚህ ሰው ፈውስ ከነቢዩ ሙሐመድ(ሰዐወ)ስም ጋር የተቆራኘ በመሆኑ አንድ ሺህ ጊዜ የነቢዩን (ሰዐወ) ስሙን ጠርታችሁ በስኒው ውሃ ላይ እንትፍ ትሉበታላችሁ ፣ ሲጠጣው ይድናል፣ አሏቸው።

   ትዕዛዙ ለቀሳውስቱ መርዶ ነበር። አንድ ጊዜ መስማት የማይፈልጉትን ስም አንድሺህ ጊዜ በአንደበታቸው መጥራትና ማውሳት ከባድ ነበር። በሽተኛው ወዳጃቸው ይንገበገባል በስቃይ ይጮኻል። የሚመርጡት ቸገራቸው። የሸሁን ትዕዛዝ ባይፈፅሙ እንዲሞት የማይፈልጉት ቄሳቸው መሞቱ ነው። እየረራቸውም ቢሆን ሀላፍትናውን ተቀበሉ። መቁጠሪያውን ተቀብለው አንድሺህ ጊዜ የአሽረፈል ኸልቅን ስም አወሱ። በስኒው ላይ እንተፍ አሉበት። ሸህ ለጋስ መድሀኒቱን ከውሃው ጋር ሰጡተ። በሽተኛው ተፈወሰ። በመጨረሻም ሸህ ለጋስ ለቀሳውስቱ የሚከተለውን መልዕክት አስተላለፉ። "ወዳጃችሁ የዳነው በነቢዩ ሙሀመድና በሳቸው ጌታ በረከት ነው።"
ሸህ ለጋስ በርካታ አስታማሪ ታሪኮችን ሰርተዋል። ገድላቸው ብቻ ራሱን የቻለ ጥናት ይፈልጋል። ምንጭ የለውጥ ቡቃያ (ከሀሰን ታጁ ግለ ታሪክ መፅሀፍ)
ሰሉ አለን ነቢይ!! (ሰዐወ)
ወገሬት!!

No comments:

Post a Comment