Wednesday, April 20, 2016

"…ብልህ ከሰው ስህተት ይማራል"

የሩዋንዳው የሁቱ እና  የቱትሲ ዘውጋዊ እልቂት እንዴት ተከሰተ? ለሚለው ጥያቄ ቀጥሎ የቀረበው…  ፅሁፍ በተወሰነ መልኩ ምላሽ ይሰጣል…

  እንደሚታወቀው የሩዋንዳ ህዝብ የ 3 ብሄረሰቦች ስብስብ ነው። እነርሱም

① ሁቱ (85%

② ቱትሲ 14%

③ ቱዋ 1%  (በጫካ የሚኖሩ)

   ☞ ፈረንሳይ ሩዋንዳን ለቤልጂየም ለቃ ስትወጣ ሩዋንዳ በቱትሲ ዘውዳዊ አገዛዝ በፍትሀዊነት ትመራ ነበር። ቤልጂየም የቱትሲውን ንጉስ በመደገፍ ለቱትሲ ህዝቦች ከሌሎች የተሻለ የትምህርት እንዲያገኙ አደረጉ።ይህም ለአብዛኛው ለሁቱ ህዝቦች ቂም አስቋጠረ። ቤልጂየም  አንዱን ብሄር ከሌላው ለመለየት የሚያስችል የነዋሪዋች የመታወቂያ ደብተር  ስራ ላይ አዋሉ። በዚህ ሂደት የሁቱ ህዝቦች የመፈንቅለ መንግስት እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር።

   የቱትሲ ህዝቦች የተሻለ የነፃነት ጥያቄ አነሱ። ጆሮ ዳባ ልበስ ያለው የቤልጂየም ቅኝ ገዥ በ1959 በሁቱዎች የተነሳውን አመፅ ድጋፍ በመስጠት የቱትሲውን ዘውዳዊ አገዛ እንዲገረሰስ አደረጉ። አገሪቷ ቀውስ ውስጥ ገባች። በቱትሲዎች ቂም የቋጠሩ ሁቱዎች ቱትሲዎች ላይ የበቀል እርምጃቸውን ጀመሩ  በጥቂት አመታት ውስጥ መቶ ሺ የሚደርሱ ቱትሲዎች ተገደሉ። የሀገሪቷ ቀውስ ከመርገብ ይልቅ ተባባሰ። በ1962 ቤልጂየም ሩዋንዳን ሙሉ በሙሉ ለቆ ወጣ። ሁቱዎች ለቀጠሉት አስር አመታት በቱትሲ ወንድሞቻቸው ላይ የበቀል እርምጃው ቀጠለ። ቤልጂየም ስራ ላይ አውላ የነበረው የመታወቂያ ደብተር ለበቀላቸው ስራን አቃሎላቸው ነበር። ቱትሲዎች  ከ1959 ጀምሮ እየደረሰባቸው ያለውን ጫናና ግድያ በመሸሽ ሀገራቸው ለቀው ወደጎረቤት ሀገራት ይሰደዱ ጀመር። ከሀገራቸው ተሰደው ከወጡ ቡሃላም ቱትሲዎች "የሩዋንዳ አብዮታዊ ግንባር" (ሩ,አ,ግ) አቋቋሙ። (ሩ,አ,ግ) የሩአግ መሪ ፖል ካጋሜ ነበር።

  በ1973 የሁቱው ርዕሰ ብሄር  ዡናቬል ሂብያሪማና በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ያዙ። ስራቸውን የጀመሩት ከዚህ ቀደም ለቱትሲዎች ያደላ የነበረውን የትምህርት አሰጣጥ አሁን ለሁቱዎች ቅድሚያ በመስጠት ቱትሲዎች በሃገራቸው በዘውጋቸው ብቻ በመገለል እንደሁለተኛ ዜጋ ለመቆጠር በቁ። ግዳያው ለጊዜው ቢቆምም አድሎው እንደቀጠለ ነበር። ይባስ ብሎ ሃብያሪማና ከሃገራቸው ተሰደው የነበር አንድ ሚልየን የሚሆኑ ቱትሲዎች የትውልድ ሀገራቸው እንዳይገቡ የሚያግድ ህግ አወጡ።

    በ1990 መጀመሪያ አካባቢ (ሩ,አ,ግ) የሩዋንዳን ድንበር አቋርጦ በመግባት ከመንግስት ታጣቂዎች ጋር ጦርነት ጀመሩ።  የህዝብ መገናኛ ብዙሃኑ በ አማፂያን ቱትሲዎች ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻውን አቀጣጠለው። ይህ ሁኔታ በሩዋንዳ የነበሩ ቱትሲዎች ላይ በማንነታቸው ከመሸማቀቅ ባሻገር ነገ ምን ይፈጠር ይሆን?  ብለው በነገ ዕጣ ፈንታቸው ሰጋት እንዲገባቸው ሆነ። በዚህም አላበቃም ሀገሩ ውስጥ የነበሩ ቱትሲዎችን ማሰርና ማሰቃየት ቀጠሉ። ርዕሰ ብሔሩ  ይህ ደርጊታቸው በአለም መንግስታት ጫና ሲፈጥርባው አስረዋቸው የነበሩ ንፁሃን ቱትሲዎች ፈታ። የአማፂያን ቡድኑ (ሩ,አ,ግ) የመንግስት ወታደሮችን እያሸነፈ ሲመጣ ወደ ሀገር እንዳይገቡ የሚያግደውን ህግ እንዲሻር ጫና ፈጠሩ። በዚህ ግርግር ውስጥ አዳዲስ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሩዋንዳ እንደ አሸን ፈሉ። ከሀገሪቱ ህዝቦች አብዛኛውን ስፍራ የሚይዙ ስራ አጥ ወጣቶች ወደነዚህ ተቋሞች ጎረፉ።

    የሃብያሪማና መንግስትም "ኢንተር ሃምዌ " ማለትም  "አብሮ የሚያጠፋ" የተባለ  የወጣቶች ስብስብ መሰረተ  በራሱም ወታደሮች አሰለጠነ።    ርዕሰ ብሄር ሃብያሪማና የአማፂያንን ጦር መቋቋም ከበዳ እንደሆነ ሲረዱ ከሩአጉ መሪ ፖል ካጋሜ ጋር  የስምምነት ውል ለመፈራረም የጦር ጄነራሎቻቸውን አስከትለው ወደ ታንዛኒያ አቀኑ። ውሉ በስደት የሚገኙ የቱትሲ ህዝቦች  ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ የሚያግደው ህግ ለመሻርና የመንግስቱ ስልጣንም እነሱንም ያሳተፈ እንዲሆን ነበር። የስምምነት የመፈራረም ሂደቱ ላይ ጄነራል ቴዎኔስቴስ ቦጎሶራ  (እጅግ ተሰሚነት የነበረው አንዱ የሩዋንዳ ነው።)  "ከቱትሲዎች ጋር መገዳደል እንጂ ስምምነት የለም" በማለት መድረኩን ረግጠው ወጡ። 

   ከዚህ ቡሃላ ሩዋንዳ እጅግ አደገኛ አደጋ የሚንዣበብባት ከተማ ሆነች። ለሰላም የነበራትን ፍላጎት በአንድ አረመኔ ጄነራል ልጇ ተነፈገች። ልጆቿ እርስ በእርስ ሲተላከቁ ለማየት ተገደደች። ከውጪ ሩአግ የመንግስትን  ጦር እያሸነፈ ድንበር እየገፋ መጣ። የሀገሪቱ አንድ ራዲዮ ለእልቂት የሚያነሳሳ ኘሮፖጋንዳ መርዙን መርጨት ጀመረ። ነጋ ጠባ ስለ ቱትሲዎች መጥፎነት አደገኛነት ብሎም ሁቱዎች ሊያምኗቸው እንደማይገባ አንፎለፎለ። ውጥረቱ ቀጠለ። በ አገር ውስጥ የነበሩ ቱትሲዎች እርዱን እምደሚጠባበቅ የመስዋዕት በግ የሞታቸውን ቀጠሮ ጠባቂ ሆኑ።

    በአንድ ማለዻ ይኸው ራዲዮ ጧቢያ… የተለመደ የጠላቻ መርዙን እየረጨ ነበር… በማሳረጊያው ላይ አንድ እንግዳ የሆነ ማስጠንቀቂያ አከለ… ማስጠንቀቂያው ይህ ነበር " እነዚህ እባቦች… በርዕሰ ብሄራችን ላይ አንድ ችግር ከፈጠሩ እዚህ የሚገኙ በረሮዎችን እንጨርሳለን… " ሲል ማስጠንቀቂያም ዛቻም የመሰለ መረጃ ተነገረ። በጥቂት ቀናቶች ውስጥ ነበር ርዕሰ ብሄሩ ከአንድ ጉዞ መልስ ኪጋሊ አየር ማረፊያ የነበሩበት አውሮፕላን  በማረፍ ላይ እያለ በከባድ መሳሪያ የተመታው።  የርሰብሄሩን ሞት ቀድሞ እንደ ቃልቻ ተንብዮ የነበረው ራዲዮ ርዕሰ ብሄር ሂብያሪማና በቱትሲዎች ተመትተው መገደላቸውን በዜናው አሳወቀ። መንግስት እልቂቱን አወጀ። ለዚሁ ተግባር ቀድሞ ያደለባቸው(ኢንተር ሃምዌ) ወጣቶችን በለው!  በለው!  እያለ… ትላንት አብሮ በኖረው በሚስቱ በጎረቤቱ በወዳጅ ዘመድ ቱትሲዎች ላይ ለቀቃቸው። በግድያ ወቅት ምንም አይነት ርህራሔ እንዳያሳዩ መጠጥ ማሪዋና የተባለ አደንዛዥ እፅ  በያሉበት በመንግስት ወታደሮች አደላቸው። ወትሮውንም ቁጥራቸው አነስተኛ የነበሩ ቱትሲዎች ዕጣ ፈንታቸው እስኪታደኑ ድረስ ማምለጥ ሆነ። ኢንተር ሀምዌ በሶስት ወር ውስጥ ወደ 1 ሚሊየን የሚደርሱ ቱትሲዎችን ጨረሰ። ይህ ሁሉ ሲሆን የአለም ማህበረሰብ ጆሮ ዳባ ልበስ አለ። በስተመጨረሻ የሩአግ አማፂያን የሩዋንዳን ዋና ከተማ ኪጋሊን ጨምሮ አብዛኛውን የሀገሪቱን ክፍሎች  ተቆጣጠሩ። ሩአግ ሲደርስ ከጥቂት ተደብቀው ከተረፉ ቱትሲዎች በቀር ሙሉ አልቀው ነበር። የመሸሹ  ተራ የሁቱዎቹ ሆነ።  ሀገሪቷ ተረጋጋች። የተያዙና ጥፋተኝነታቸው የተረጋገጠ  ሁቱዎች በአለም አቀፍ ፍርድ ቤትና በሩዋንዳ ባህላዊ ፍርድ ስርአት ቅጣታቸውን አገኙ። ከዚህ ቡሃላ ሩዋንዳ ሁቱ ቱትሲ የተባሊ ልዩነቶችን አስወገደች። ለሁሉም ህዝብ አንድ አይነት መታወቂያ አዘጋጀች። ሞኝ ከስህተቱ! ብልህ ከሰው ስህተት ይማራል! በማለት ጨረስኩ።

ምንጭ - Left to tell ኢማኪዩሌ ኢሊዛጊባ
ትርጉም በመዘመር ግርማ

No comments:

Post a Comment