Tuesday, April 5, 2016

ክቡር መንፈሴ ሆይ!

አንተው ህግ አርቃቂ
አንተው ፍርድ አፅዳቂ
የወህኒው ባለቤት
የወህኒው ጠባቂ
ደካማው ሰለባህ
በሀይልህ ስር ታስሮ
ያመልጥ ይሆን ሰብሮ?
ይበቀለኝ ዞሮ
ምን ያስብ ምን ያቅድ
ምን ይክብ ምን ይንድ
ብለህ በማውጠንጠን
እረፍት ከምታጣ
ምርኮኛህን ፈተህ
አንተው ነፃ ውጣ።

☞በዕወቀቱ ስዩም

1 comment: