Tuesday, April 5, 2016

ከወሪሳ መፅሀፍ … ዓለማየሁ ገላጋይ

"አንድ ታሪክ ለጫውትህ" አሉ አዛውንቱ ። "እሺ ደስ ይለኛል… ☞ በእምዬ ሚኒሊክ ዘመን አባ ንጠቀው አባ መንትፈው የተባሉ የዘራፊ ጎሳ መሪ ነበሩ አሉ። አባ ንጠቀው በአፄው የሚታደኑ ሰው የነበሩ ቢሆኑም ቅሉ በኢጣሊያ ወረራ ዘመቻ ባደረጉት ንቁ ተሳትፎ አፄው ሚስጥራዊ እውቅና ሰጥተው ከቤተ መንግስታቸው አቅራቢያ መሬት በመስጠት አሰፈሯቸውና አንድ ተጉለቴ (ሰላይ) አሰማሩባቸው። ☞ተጉለቴው አባንጠቀውን በገቡ በወጡ ቁጥር እየተከታተለ መፈናፈኛ አሳጣቸው። አንድ ቀን አባ ንጠቅ ለተጉለቴው "አንተ ሰው ዉቃቢዬ የሚከታተለውን አይወድም ጨርቁን አስጥሎ ያሳብዳል ይሉታል። ተጉለቴውም ግድ የለም እኔን የሚዳፈር ውቃቢ የለም ሲል ይመልሳል። በል እንግዲህ በወር 1 ውስጥ እናያለን ይሉና ስራቸውን ይጀምራሉ። "እሺ" አልኩ ታሪኩ ጥሞኝ። አባንጠቀው ቀጭን ረጅም አጠና ጫፍ ላይ ቁራጭ ቆርቆሮ ይመቱበትና ረጅም አካፋ መሰል እቃ ያደርጉበትና። ተጉለቴው ለእዳሪ (ለመፀዳዳት) የሚወጣበትን ሰዓት ተደብቀው ይጠብቁት ጀመር። ተጉለቴው ለእዳሪው መጥቶ መቀነቱን ፈትቶ ተቀመጠ። አባ ንጠቀው የያዙትን ቀጭን አጣና ወደ ሚቀመጥበት ስፍራ እየገፉ አነጣጥረው ያኖሩታል። ተጉለቴዉ ፋንዲያዉን አራግፎ ሱሪውን ሊታጠቅ ብድግ ሲል አጠናውን በመሳብ ፋንዲያውን ሰወሩበት። ተጉለቴው እየታጠቀ ፍጉን ቢያይ የለም። እንዴ "አርቼ… ጠፋ ጉድ!ጉድ "እያለ ጮኸ። አላፊ አግዳሚ ነዋሪው "አሩ ተገኘ?" እያሉ በማሽሟጠጥ ሲጠይቁት። "የለም ጠፋቶ ቀረ!" እያለ ይመልሳል። ተጉለቴው እውነትም አባ ንጠቅ እናዳሉትም ወር ሳይሞላ ጨርቁን ጥሎ አበደ። ታዲያ መንደርተኛው ለአባ ንጠቅ ቅኔ ተቀኘ። > ከሼባው ጋር ሁለታችንም ተያይዘን ሳቅን… ምንጭ–ወሪሳ

No comments:

Post a Comment