Tuesday, June 14, 2016

"አ ን ዲ ት ዳ ቦ!"

"አ ን ዲ ት   ዳ ቦ!"
#ሳteናw

… ከዛፏ ጥላ ስር የተሸከመውን እቃ አውርዶ እረፍት ለማድረግ ተቀመጠ። በጣም ድካም የተሰማው ነስሩ ከወትሮው በላቀ ሁኔታ ፈጣሪውን…

"ያ አላህ አሁን አንተ እኔን አንዲት ዳቦ መረዘቅ አቅቶህ ነው በእንዲህ ያለ ከባድ ስራ የምታኖረኝ? " ሲል አማረረና ትንሽ ድካሙ ቀለል ሲልለት ከባዱን እቃ የተባለበት ለማድረስ መንገዱን ቀጠለ…
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★

  ነስሩ አብደላህ ይባላል። ሙስሊም ነው (የእስልምና እምነት ተከታይ) ነገር ግን በእምነቱ) ጠንከር ያለ አማኝ አይደለም። ወንደላጤ ወጣት ቢሆንም እጅግ ዝቅተኛ የገቢ መጠን ካላቸው ሰዎች ይመደባል። የእለት ጉርሱንም የሚሸፍነው ቀን ቀን ተሯሩጦ ከሚያገኘው የጉልበት ስራ ነው። ነስሩ ሁልጊዜ አላህ በሰጠው ጤንነት እና ጉልበት ከማመስገን ይልቅ ፈጣሪውን አብዝቶ ያማርራል። የጤንነት ዘውዱ ለሰው እንጂ ለራሱ ስለማይታየው ነበር ከማመስገን መቦዘኑ።

አንድ ቀን እንዲህ ሆነ። ነስሩ የእለት ጉርሱን የሚሸፍንበትን የጉልበት ስራውን በመጠባበቅ ላይ እንዳለ። ስራውይመጣና ከባድ ክብደት ያለው እቃ ከአንድ ስፍራ እንዲያደርስ ተነጋግሮ  እቃውን ተሸከሞ ከተባለበት ቦታ ለማድረስ ጉዞውን ጀመረ :: እቃው ከባድ ከመሆኑም በላይ የሚያደርስበትም ቦታ ትንሽ ራቅ ስለሚ የተወሰነ መንገድ ከተጓዘ ቡሃላ እጅግ ስለደከመው አንድ ዛፍ ጥላ ካለበት ስፍራ ላይ… እረፍት ከወሰደ ቡሃላ እቃዉን አደረሰ።

ከዚህ ቡሃላ ያለውን ገጠመኝ ነስሩ በራሱ አንደበት ይተርክልናል…

" እቃውን አድርሼ በመመለስ ላይ ሳለሁ መንገድ ላይ የተወሰኑ ጎረምሳዎች እርስ በእርስ ሲደባደቡ ደረስኩኝ:: እኔም ለመገላገል መሀከላቸው ገባሁ:: ጎረምሶቹ በከፍተኛ በንዴት ውስጥ ስለነበሩ. ለማገላገል መግባቴን ሳይገነዘቡ ለአንዱ ወገን አጋዥ አድርገው ስለቆጠሩኝ ይወቅጡኝ ገቡ እኔም በመናደድ እራሴን ለመከላከል በሚል ሰበብ ያገኘሁት ላይ ጥቃት ማድረስ ጀመርኩ። ይህ በንዲህ እንዳለ ከየት መጡ ያልተባለ የመንግሥት ታጣቂዎች ከበቡን። ሁላችንም ላይ የዱላ ውርጅብኝ አወረዱብን። አረ እኔ ምንም የማውቀው ነገር የለም ለማገላገል ነው የገባሁት" ብልም ሰሚ አላገኘሁም።  ይባስ ብሎ አንደኛው ታጣቂ "እሱም ሲሰነዘር አይቸዋለሁ " አለና መሰከረብኝ:: የመንግስት ታጣቂዎቹ ሁላችንንም እጃችንን በካቴና በመቆለፍ ይዘውን ወደ ጣቢያ ወሰዱን:: ጣቢያው እንደደረስን አንድ በአንድ ወደ ቃል መቀበያ ቢሮ እያስገቡ ቃላችንን ተቀበሉና ወደ ማረፊያ ክፍል(እስር ቤት) አስገቡን። የታሰርንበት ክፍል ቆሻሻ ከመሆኑም በላይ የሚከረፋ ሽታ የሚሸትበት ነው :ወለሉ ላይ የተነጠፉት እጅግ ስስ ፍራሾች በእድፍ ከመጥቆራቸው የተነሳ የመጀመሪያ መልካቸውን ለመለየት ይቸገራል:: በዚህ ክርፋታምና እጅግ ቆሻሻው ክፍል ለረጅም ሰአት ቆየን ምንም ምግብ ሰላልቀመስኩ እጅግ ራበኝ። በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳለን የታሰርንበት ክፍል በር በሃይል ተገፍቶ ተከፈተ። አንድ የእስርቤቱ ዘብ ነበር በእጁ አንዳች ነገር ያለበት ተለቅ ያለ ከረጢት ይዟል። በሀይለ ቃል "እያንዳንድህ ተነስና ተሰለፍ " ሲል አምባረቀ። እኛም ለምን ተነሱ እንዳለ ባይገባንም እንደተባልነው አደረግን። እንዳለን መሰለፋችንን እንዳየ…

"የያዘውን ከረጢት በመክፈት ለአንድ ሰው የሚበቃ መጠን ያለው ዳቦ አወጣና ከሰልፉ ፊት ካለው ግለሰብ በመጀመር ለእያንዳንዳችን መስጠት ጀመረ። ለሁላችንም ዳቦውን አዳርሶ እንዳበቃ በገባበት አኳኋን ከክፍሉ በመውጣት በሩን ጠርቅሞብን ሄደ:: ሁላችንም የተሰጠንን ደረቅ ዳቦ በደረቀው አፋችን እያላመጥን ዳቦውን በላን። የታሰርንበት ቀን ቅዳሜ ስለነበር በ24 ፍርድ መቅረብ ቢኖርብንም ቀጣዩ ቀን የእረፍት ቀን በመሆኑ መቅረብ ስላልቻልን የእረፍቱን ቀንእዛው እስር ቤት አሳለፍን። ልክ በትላንትናው ሰአት ዳቦ የሚያድለን የጥበቃው አባል በሩን ከፍቶ ገባና ዳቦ ያድለን ጀመር።

በዚህ ጊዜ አንዳች ነገር ትዝ አለኝ አላህን ያመረርኩባት ቃል

" ያ አላህ አሁን አንተ እኔን አንዲት ዳቦ መረዘቅ አቅቶህ ነው በእንዲህ ያለ ከባድ ስራ የምታኖረኝ? "ያልኳት ቃል::

  ይህ ሁሉ እሱን በሰጠኝ መልካም ጤንነት  ባለማመስገኔና በማማረሬ በገዛ እጄ ያመጣሁት መከራ መሆኑ ተገለፀልኝ። ወደ ጌታዬ ተመለስኩ ያረቢ! አጥፍቻለሁ ማረኝስል ተማፀንኩ ድጋሚም አላህን ላለማማረር ለራሴ ቃል ገባሁ። በሰጠኝ ጤንነትና ጉልበት ማመስገን እንዳለብኝ በሚገባ አወኩ እሱን በመገዛትም (በኢባዳ) መጠንከር እንደሚገባኝ ራሴን አሳመንኩት። ከዚህ እስር ያውጣኝ እንጂ ከወጣው ቡሃላ በዲኔ እንደምጠነክር ላላማርረው እና በሰጠኝ ሲሳይ ላመሰግነው ለጌታዬ ቃል ገባሁ እንዲህ ካደረኩ ቡሃላ ቀለል አለኝ። በዚያን ሌሊት ነቢዩላህ ዩኑስ ከአሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ሳሉ ያደረጓትን ዚክር "ላ ኢላሃ ኢላ አንተ ሱብሃነከ ኢኒ ኩንቱ ሚነ ዟሊሚን " ስዘክር አደርኩ:: በማግስቱ ሰኞ ፍርድ ቤት ቀርበን የዋስ መብቴ ተጠብቆልኝ ከእስር ተፈታሁ:: አልሃምዱሊላህ. ያሳለፍኩት የእስር ቆይታዬ እጅግ ብዙ ትምህርት ሰጥቶኛል ወደ ጌታዬ እንድመለስ ሰበብ ሆኖኛል አልሃምዱሊላህ።"

☞የነስሩ ገጠመኝ እጅግ አስተማሪ ነው:: እኛም ከገጠመኙ ብዙ የምንማራቸው ነገሮች አሉ አይደል? አዎ! አለ ,በሰማነው ተምረን የምንተገብር ያድርገን!!።
ወገሬት!!

ምንጭ ሼክ ኢብራሂም ሙሐመድ አፍሪካ ቲቪ ላይ ከተናገሩት አስተማሪ ቂሳ:: ትምህርቱን በዚህ መልክ ለማስተላለፍ እንዲመች ተደርጐ ጭማሪ አገላለፅ ተጠቅሜአለው!!

No comments:

Post a Comment