Friday, June 17, 2016

"አ ጄ ክ ስ ዘ ግ ሬ ት"

"አ ጃ ኢ ቦ "
#ሳteናw

  በምን ትዝ እንዳለኝ አላውቅም ብቻ ትውስታዬን ቃላት በቃላት እየሰካካው በፅሁፍ ማስፈር ጀመርኩ። ከመንደሬ ሰልባጅ ጫማ ሻጭ ከነበረው አጃይቦ ጋር በተያያዘ ፈገግ የሚያደርግህን ስር ነቀል ቀልድ ላጫውትህ ወደድኩ…
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
…  በተንኮለኛ ጓደኛው … የግድግዳው ሰዓት መዘውር ከጊዜው ሁለት ሰአት  ሆን ተብሎ ወደ ኋሏ ተሞልቷል። ይሄን ያላወቀው አጃኢቦ የሱሁር ሰአት ገና ሁለት ሰአት ይቀረዋል በሚል ጉንጩን እንደ የመኒ  ወጥሮ ሲቅም!። በመስኮት በኩል የንጋት ውጋገን ተመለከተ… እሪሪሪ ብሎ መጮህ ቃጣው። ሁሌም በሸር የሚጫወትበትን ጓደኛው ከድሾን እያማረረ በጉንጩ የወጠረውን ጫት ተፍቶ ወደ ስራ ወጣ…
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
   "አጄክስ ዘ ግሬድ፣ የሃምሳ ሰው ግምት፣ የሺህ ሰዉ ዋስ"  ዘወትር እራሱን የሚያወድስባት ከአፉ የማትጠፋ ንግግር ነበረችው። የሰፈሬ ሰልባጅ ጫማ ሻጭ የነበረው አጃኢቦ ተማም። አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች የጫማ አቅርቦት በማቅረብ ይታወቃል። በተጨማሪም አንድ አግር ብቻ ላላቸው ወገኖች አንድ እግር ጫማም በመሸጥ ይታወቃል። ሌላው
አጄክስ ባለበት ፆታዊ ለከፋ ነበረ። አጄክስ ባለበት ጨዋታ ነበረ። አጄክስ ባለበት ጫት ነበረ። አጃይቦን ለየት የሚያደርገው ፆታዊ ለከፋው ያለ አድልኦ መፈፀሙ ነበር። በአጄክስ ለመለከፍ እድሜዋ ገፋ ያላለች ሴት መሆን በቂ ነው። ኮንጎ ትልበስ ሂልስ ሂጃብ ትጠምጥም ፀጉር ትልቀቅ ፣የቤትም፣ የመንግስትም ሰራተኛ ትሁን ብቻ እኛ ሰፈር ከመጣች ወይ ካለፈች በቃ ያለጥርጥር አጄክስ ለክፏታል። በአጄክስ ለመለከፍ ሆን ብለው በአጠገቡ የሚያልፉ እንደነበሩ ሁሉ የተደባደቡትም ነበሩ።
አጄክስ በሳቅ ፈጣሪነቱ፣ ሰው ይወደዋል ያቀርበዋል፣ ያበላዋል  ያጠጣዋል፣ ያስቅመዋል፣ይጋብዘዋል፣ አንቦ ውሃ እንደ ሻንፓይን ነቅንቆ  በላዩ ላይ ያርከፈክፉበታል፣ ይዝናኑበታል። አጄክስ በመንደሬ ሰው ይወደዳል። በተለይ ሀብታሞች። ከነዚህም ውስጥ ከድሾ ይገኝበታል። ከድሾ ከአጄክስ በጫወታ ቢበልጥ እንጂ አያንስም፣ በተለይ በተንኮል የሚያክለው አልነበረም።

   ታዲያ አንድ ቀን ጫማዎቹን ከጊቢያችን በር ላይ ዘርግቶ ይቅማል። በአዋራ ያደፉት እያነሳ ይወለውላል። ቀኑን ምንም ጫማ ስላልሸጠ ሙዱ ተጦልቧል። ካሁን አሁን ገዢ የመጣ እየመሰለው አላፊ አግዳሚውን በአይኑ ይለማመጣል ከሱ አለፍ ብሎ ከድሾ ከጓደኞቹ ጋር ይቅማሉ። ሙዱ የተጦለበውን አጄክስ ይበልጥ ለማናደድ አጋጣሚውን ሆን ብሎ ይጠብቃል። በዚህ ቅፅበት አራት የኔ ቢጤዎች(ባላ የመሰለ ዱላ የያዙ ገሪባዎች) አጃይቦን አልፈው ወደነ ከዲሾ መጡ። ምጽዋትም ጠየቁ። ከድሾ ለያንዳንዳቸው ብርና ከሚቅመው ጫት ዘግኖ ሰጣቸው። መረቁት!።አይገልፀውም። ቀጥሎ ጫማ ትፈልጋላችሁ ሲል ጠየቃቸው። አዎ ሲሉ። እዛ ጋር ከተደረደረው ጫማ የሚበቃችሁን መርጣችሁ ውሰዱ እኔ እከፍላለው  ይላቸዋል። የደግነቱ ወሰን የመጠቀባቸው እንዚህ የኔ ቢጤዎች ምርቃታቸውን ከጨረሱ ቡሃላ። ጫማ መርጠው ለመውሰድ ወደ አጃኢቦ ሄዱ። ተገጥግጠው ከተደረደሩ ጫማዎች የሚሆናቸው እያነሱ መለካት ያዙ። አጄክስ የሚገዙት መስሎት በግርምት ይመለከታቸዋል። ሁሉም የሚበቃቸው ጫማዎች ከተጫሙ ቡሃላ በቃ እሱ ነው የሚከፍለው አሉት።

"ማን?" አጄክስ በግርምት እየጠየቀ ከፋዩን በአይኑ ፈለገ።

"ይኸው እሱ!" ብለው ከድሾን ጠቁመውት መንገድ ሊጀምሩ ሲል "

"አዉልቅ እናት ል**" ብሎ ትልቅ ድንጋይ አንስቶ ሊለቅባቸው ሲል… ገሪባዎቹ በድንጋጤ የተጫሙትን ጫማ አውልቀው በባዶ እግራቸው ቀደዱት። ስፅፈው እንኳ በጣም እየሳኩ ነው።

አንድ ልጨምርና ልንካው። በሰማኒያዎቹ ውስጥ ነው በአንድ የረመዳን ምሽት ደግሞ እንዲህ ሆነ። … ከድሾ አጃይቦን ጨምሮ ከብዙ የሰፈር ልጆች ጋር በቤቱ አዳር ለመቃም ሙሉ ወጪውን ስፖንሰር በማድረግ ይዟቸው ሄደ። ሲቅሙ ሲስቁ አመሹ። አጃኢቦ ለሽንት ሲወጣ የግድግዳውን ሰዓት አውርዶ ሁለት ሰአት ቀንሶ ሞላው ይህን ከአጃኢቦ በቀር ሁሉም አውቋል። የሱሁር ሰአት ሲደርስ በተራ ተራ ሁሉም ኪችን እየሄዱ በልተውና ተጉመጥሙጠው አጠገቡ በመቀመጥ ጥርሳቸውን መፋቅ ጀመሩ። ደከመኝ በሚል ሰበብ ወደመኝታቸው ሄዱ። አጃኢቦ ሆዬ አረ ገና ነው ሁለት ሰአት ይቀረናል ቢላቸውም። ሰበብ እየሰጡት ስቀው ገብተው ገብተው ተኙ። አጄክስ በቻውን ቀረ። ሁሉም ትተውት የተነሱትን ጫት ማመንዠጉን ቀጠለ። የሱሁር ሰአት ገና ሁለት ሰአት ይቀረዋል በሚል አስፍቶ ሲቅም! ነበር በመስኮት በኩል የንጋቱን ውጋገን ተመለከተ። ከድሾ እንደሁሌውም እንደተጫወተበት ገባውና… ተሳድቦ ተሳድቦ ሲወጣለት ወጥቶ ሄደ። ምስኪን አጄክስ!! ዛሬ በህይወት የለም! ሊሞት አካባቢ ግን አድርጎ የማያውቀውን የአማኝ ተግባራት መፈፀም ጀምሮ ነበር። በአጭሩ መጨረሻው አምሮለት ነበር። በጉርምስና ግፊት ቀይ መስመሯን ያለፈ ቀልድ የቀለደው ከድሾንም አላህ ይቅር ይበለው!! ለአጄክስም ጀነተል ፊርደውስ ይወፍቀው ዘንድ ሁላችሁም ፀሎት በዱኣ እትዘንጉት!!
ወገሬት!!

No comments:

Post a Comment